የዋድላ ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት
16-06-2025 05:50amየዋድላ ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ወቅቱን እና ዘመኑን በዋጀ መልኩ ከቴክኖሎጂ ጋር በመራመድ አገልግሎትን ማዘመን ተገቢ መሆኑን በጽ/ቤቱ በኩል በአጽንኦት ተወያይቷል ወደ ስራም ለመግባት ቅድመ ሁኔታ እያመቻቸ ነው። የዋድላ ወረዳ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መንጥር ዘሩ ኮን ከተማ ላይ የሐሙሲት ከተማን ባለሙያዎችን እና ስራ አስኪያጆችን በመጥራት ውይይት እና አጠር ያለ ስልጠናም ስለ ሲስተሙ አተገባበር እና የቀጣይ ቀዳሚ እና አስፈላጊ ተግባር መሆኑን ተገንዝቦ ስራ ደሚሰራ ጽ/ቤቱ ገልጿል። የመረጃ መበላሸት፣የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋን ለመከላከል ሲባል ወቅቱ የሚጠይቀውን የቴክኖሎጂ አማራጭ በመጠቀም ወደ ስራ ለመግባት ዝግጁ መሆናቸውን እና አገልግሎት አሰጣጡ በሲስተም የታገዘ እንዲሆን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት እንዲያግዙን መረጃ ማለት ሃብት ነው ሃብታችንን ደግሞ በተገቢው ሁኔታ በመያዝ ለህዝብ ማቆየት እና አገልግሎቱን ማዘመን እኛም ህብረተሰባችንም የምንፈልገው ነው በማለት የስልጠናው ተሳታፊዎች ባለሙያወች እና ስራ አስኪያጆች ገልጸዋል