የሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ሲቪል ምህንድስና ቡድን የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ።
02-11-2025 18:10pm(ግንቦት 22/2017 ዓ.ም- ሰሜን ወሎ ከመልመ) የሰሜን ወሎ ዞን ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ የሲቪል ምህንድስና ቡድን በ2017 በጀት ዓመት ሊያከናውን በእቅድ ከያዛቸው ተግባራት መካከል አንዱ ለከተሞችና ወረዳ ህንፃ ሹሞችና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ነው በዚሁ መሰረት፦ 1.በህንፃ አዋጁ፣ ደንቡና ማስፈፀሚያ መመሪያዎች እንዲሁም በተሻሻለው የህንፃ መመሪያ 2.በነባር ግንባታ መመሪያ 3.የካሬ ሜትር መገመቻ ዋጋና ከስመ ንብረት ዝውውር መመሪያ ጋር ተጣጥሞ ስለሚሰራበት አግባብ በሚሉ ርዕሶች በመምሪያው ስር ካሉት ከሁሉም ከተሞችና ወረዳዎች ለመጡ ተሳታፊዎች በተደራጀ አግባብ ስልጠናው ተሰጥቷል።