👤👤Staff
Home About Us Main point Service Job Vacancy Materials Comment

"Please wait"
እባክወ በትዕግስት ይጠብቁ!

የጋሸና ከተማ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጸጋ ውቤ ለትንሳኤ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል

05-04-2026 12:25pm

የጋሸና ከተማ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጸጋ ውቤ የትንሳኤን በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ባማስቀደም ጀምረው የከተማዋን ዋናዋና ገጽታወችን እና የቀጣይ አቅጣጫንም አስቀምጠዋል። ጋሸና ከተማ ከጥር 2013 ዓ.ም ጀምሮ ወደከተማ አስተዳደርነት አድጋለች ከተማችን በ4ቱም አቅጣጫ ሃገር አቋራጭ መስቀለኛ መንገድ ያላት ከጅቡቲ ወደብ የሚወጡ በርካታ ተሽካርካሪ ወች የሚያርፉባትና ወደፊትም የደረቅ ወደብ መሆን የምትችል ከተማ ናት ለ9 ወረዳወች የመብራት ሃይል አገልግሎት መስጠት የሚችል የመብራት ሳብስቲሽን አላት በ4ቱም አቅጣጫ ወደተለያዩ ከተማወች እና ታሪካዊ ቦታወች የቱሪስት እንቅስቃሴ የሚደረግባት ከተማ በመሆኗ መስለቀለኛዋ የቱሪስት በር ትባላለች 118.74 ሄክታር መሬት ክላስተርድ የሆነ የኢንዱስትሪ መንደርና የኢንቨስትመንት አገልግሎት የሚውል መሬት አለ። ጋሸና ከተማ ወደፊት ለመልማት ትልቅ ዕድል ያላት እና መስቀለኛ መንገድ ላይ ያለች እጅግ በጣም የተመቸ የአየር ንብረት እና መልካምድር ያላት በመሆኗ ማንኛውም ባለ ሃብት ወደዚህ ከተማ ቢመጣ በፍጥነት ለማስተናገድ ዝግጁ መሆናችንን ለመግለጽ እወዳለሁ። በድጋሜም እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ።

loading

ይህ መረጃ 65 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----

   ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇    👇    👇   ሚዲያወች በመጫን Share..

Comment Form