"Please wait"
እባክዎ በትዕግስት ይጠብቁ የኢንተርኔትዎ ዳካማ መሆን ነው!

Home About Us Main point Service Job Vacancy Comment

ጋሸና ከተማ

13-07-2026 16:10pm

December 1, 2021
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን ጋሸና ከተማ አስተዳደር አነስተኛ ከተማ ናት ጋሸና፡፡ ከተማዋ ደቡብ ጎንደርን በስተምእራብ፣ ወልዲያን በስተምስራቅ፣ ላሊበላን በስተሰሜን እና ወገልጤናን በስተደቡብ የምታዋስን ስትራተጂክ ከተማ ናት፡፡
አሁን ባለው መረጃ መሰረት በከተማዋ በግዜያዊነት የሚኖሩ ዜጎችን ጨምሮ ወደ 22 ሺህ የሚጠጋ ነዋሪ ይኖርባታል፡፡ ይህች ተራራማ በሆነ ቦታ ላይ የተቀለሰች ከተማ ደጋማ የሆነ የአየር ንብረት ሲኖራት፣ ከባህር ጠለል በላይ በ2977 ሜትር ከፍታ ላይ ትገኛለች፡፡
ከተማዋ ከጂኦግራፊያዊ አቀማመጧ እና መልካምድሯ ጋር በተያያዘ ወሳኝ ስፍራ የሆነችበትም ምክንያትም የስድስት በሮች መተላላፊያ መስመር በመሆኗ ነው። ይህም በስተምእራብ ወደ ጎንደር፣ በስተምስራቅ ወደ ወልድያ፣ በስተደቡብ ወደ ወገልጤና (ደላንታ) ይገባና ከወገልጤና ወደ ደሴና ወደ ምእራብ ውሎ (ተንታ፣ አቀስታ፣ ቦረና) ያስገባል። በተጨማሪም በስተሰሜን በኩል ወደ ላሊበላ፣ አይና ቡግና፣ ወደ ሰቆጣና ወደ ኮረም (ትግራይ) ያስገባል። ይህም ጋሸናን የኮረም፣ የሰቆጣ፣ የወልድያ፣ የጎንደርና የደሴ መግቢያ በር በመሆንዋ ለወታደራዊም ይሁን ኢኮኖሚዊ ጠቀሜታዋ የጎላ ነው።
ይህንም በዝርዝር ለማየት፣ ከተማዋ አዋሳኝ የትራንስፖርት አማራጭ የሆነችበትም ምክንያት ለማየት ያክል ከወልድያ ወደ ጎንደር የሚወስደውን ዋና የአስፓልት መንገድ፣ ከጋሸና ወደ ወገልጤና የሚወስደው መንገድም ገርማሜ ሲደርስ በስተምስራቅ የደሴን አስፓልት በስተምእራብ ደግሞ የወረኢሉን ዋና አስፓልት መዳረሻ በመሆኑ ነው፡፡ በተለይም ከጋሸና ተነስቶ በላሊበላ መስመር ላስታን፣ አይና ቡግናን፣ ግደንን፣ እልፎ ቤላ ሲደርስ በስተሰሜን ሰቆጣን በስተምስራቅ ደግሞ ኮረምን የሚያዋስን መንገድ አለው፡፡
የሰቆጣን መስመር ይዘን ስንሄድም፣ እስከ አግቤ/ አቢ አዲ (ትግራይ) ድረስ የሚያስኬድ እና ዋናውን የአስፓልት መስመር የሚያዋስን መንገድ የያዘች ከተማ ናት፡፡

loading

ይህ መረጃ 5 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----

   ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇    👇    👇    ሚዲያወች በመጫን Share..

Comment Form