"Please wait"
እባክዎ በትዕግስት ይጠብቁ የኢንተርኔትዎ ዳካማ መሆን ነው!

Home About Us Main point Service Job Vacancy Comment

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው አደረሳችሁ❗❗

13-07-2026 15:51pm

አዳም ዕፀ በለስ በልቶ ከገነት ከተባረረ በኋላ ለ5500 ዘመን ያህል በሲኦል ውስጥ ሆኖ ኢየሱስ ክርስቶስ የገባለትን ቃል ኪዳን በተስፋ በመጠባበቅ ላይ ሳለ አምላኩ ብዙ መከራናና ህማም ተቀብሎ በመስቀል ተሰቅሎ በገባለት ቃል መሰረት አዳነው። ያ የውርስ ሀጢያት አሁን በምድር ላይ ለምንኖር ለእኛም ጭምር ሳይተርፍ አዳም ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ ወጣ። የእሱ ነጻ መውጣት ለእኛም ተረፈን።
ከኢየሱስ ክርስቶስ ትንሳኤ የምንማረው ከብዙ መከራና ስቃይ በኋላ ትንሳኤ አለ ከብዙ ተጋድሎ በኋላ ድል መቀዳጀት አለ። ያ ሁሉ ግፍና መከራ ሲደርስበት አንዳችም ነገር በቂም በቀል አልተሞላም አምላክ ነኝ ብሎ ሊያጠፋቸው አልሞከረም ይልቁንም የሚገርመው "የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ እንጅ ። አዳም 5500 ዘመን በጨለማ ግዞት አለም ቢኖርም አምላኩ የነገረውን የተስፋ ቃል በመጠበቅ ከጨለማ አለም ግዞት ወጣ በትንሳኤው ብርሀን ተዋጀ። ድልንም ተቀዳጀ።
ከዚህ የምንማረው የገጠመንን ፈተናና የሰላም እጦት በትዕግስትና በተስፋ በፍቅርና በአንድነት ችግሮችን ሁሉ እየተጋፈጥን አሁን ካለንበት ሁከትና ብጥብጥ ጦርነትና ጥላቻ መውጣት የምንችል መሆናችን ነው። ከጨለማ በኋላ ብርሀን ከሞት በኋላ ትንሳኤ አለ።
የኢየሱስ ክርስቶስ ይቅር ባይነት የሚያስተምረን ምንም እንኳን የተለያየ ቅራኔና ፍላጎት ቢኖረንም ይቅርታ ፍቅርና አንድነት ግን ወሳኝ መሆኑን ነው። ሀገራችን በተለይ ክልላችን አሁን ከገጠመው ችግር ማውጣት የሚቻለው በፍቅር በይቅርታና በድርድር በውይይት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
በድጋሜ እንኳን ለብርሀነ ትንሳኤው አደረሳችሁ❗❗
በዓሉ የሰላም የይቅርታ የመተሳሰብና የአንድነት እንዲሆንልላችሁ እመኛለሁ

loading

loading

ይህ መረጃ 2 ጊዜ በተለያዩ ሰዎች ታይቷል ---) (----

   ይህንን መረጃ ከታች ባሉት 👇    👇    👇    ሚዲያወች በመጫን Share..

Comment Form